የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማህበር የኮቪድ-19ን ለመከላከል የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሊያደርጉ ነው

0
278

https://news.et/wp-content/uploads/2020/04/Travel-Vlog-YouTube-Thumbnail-2020-04-24T200755.536.jpgየግል ከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማህበር የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማህበር የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል 25 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

የማህበሩ የቦርድ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሞላ ጸጋዬ ከማህበራት ገንዘብ የተገኘውን የ2.7 ሚሊዮን ብር ጨምሮ ህንጻዎችን፣ ተሽከርካሪዎችን፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ፣ የምግብና የጽዳት ዕቃዎችንና የጤና ተቋማትን ነው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ያስታወቁት፡፡

ማህበሩ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚፈጠሩ የቴክኖሎጂና ሌሎች አጋር መድረኮችን በመጠቀም ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ጥረት እንደሚደረግም አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ተቋማት ከተማሪዎች የሚያገኙትን ገቢ የወቅቱ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገና ማህበረሰቡን በማይጎዳ የወርሃዊ ክፍያቸው በመግባባት ስሜት እንዲፈጸም በተለይም በቀጣዩቹ ሶስት ወራት የተማሪዎች ክፍያ ላይ ቢያንስ የ25 በመቶ ቅናሽ እንዲያደርጉ እንዲሁም በሌሎች አገልግሎቶች ላይ ቅነሳ ወይም ስረዛ እንዲደረግ ቦርዱ መወሰኑን የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ተባባሪ ፕሮፌሰር ወንዶሰን ታምራት ገልጸዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here